menstruation period
menstruation period

የወር አበባችን ስለ ጤናዎ የሚነግርዎት 6 ነገሮች

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)

የወር አበባ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በግልጽ እንዲወራ ከማይፈልጋቸው ጉዳዩች አንዱ ነው ነገር ግን በሰፊው ልናወራበት ልንወያይበት የሚገባ ጉዳይ ነው በተለይ የጤናዎ ጉዳይ ሲሆን፡፡ ስለ ወር አበባ የሰሙት ወይም እንዲያዉቁ ያደረገዎት ያደጉበት ማህበረሰብ ወይም አንደ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እያሉ ሊሆን ይችላል፡፡

ይህ በየወሩ እየመጣ የሚጎነኝንን እንግዳ ስለ ጤናችን በማንኛውም እድሜ ላይ ለሚገኙ ሴቶች የትኛው ጤናማ እንደሆነ እና እንዳልሆነ እንዴት እንደሚነግረን አብረን እንከታተል

1. የወር አበባ ህመም
በህክምና ቃላት አገላለጽ ዲስሜኖሪያ ይሉታል በወር አበባ ጊዜ የሚከሰተውን የሆድ ቁርጠት ለመግለጽ ይህ ህመም በወር አበባ ጊዜ የማህፀን ግድግዳዎች መርገፍ/መፍሰስ ነው፡፡ ይህ ህመም በ50% ሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን የፕሮስታግላንዲን ሆርሞን መብዛት ለዚህ ህመም ተጠቃሽ ነው፡፡ ፕሮስታግላንዲን ሆርሞን ለሚከሰተው ህመም እና የሰውነት ማበጥ/መቅላት ነው፡፡
በታችኛው የሆድ ክፍል ላይ ከባድ የቁርጠት ህመም ካለብዎት ከፍተኛ የጤና ችግር እንዳለብዎት ጠቁሚ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ኢንዶሜትሪዮሲስ ይባላል ይሄ ችግር ያለባቸው ሴቶች የማህፀን ግድግዳቸው ከማህፀን ውጪ በማደጉ ምክንያት የወር አበባ በሚፈስበት ጊዜ የሚወጣበት/የሚፈስበት ቦታ ያጣል፡፡ በዚህ በሽታ ከ7-10% የሚሆኑ ሴት እህቶቻችን ይሰቃያሉ፡፡

2. የወር አበባ ቀለም/መልክ
የወር አበባ መልክን ማወቅ ስለ ጤናዎ ሁኔታ ብዙ ነገር ይናገራል፡፡ሆርሞኖች በ4ኛው ሳይክል ላይ ይለዋወጣሉ ይህም በወር አበባ ቀለም እና ይዘት ላይ ለውጥ ያስከትላል፡፡ ሴቶች በወር አበባ ጊዜ 3 ዓይነት የቀለም መደቦች ያስተዉላሉ እነዚህም የብሉ ቤሪ፣እንጆሪና ክሬን ቤሪ ቀለም ናቸው፡፡
የተጋገረ ብሉ ቤሪ ቀለምና ይዘት ያለው የወር አበባ ከፍተኛ የኢስትሮጂን መጠን እንዳለው ያመለክታል የዚህ ሆርሞን መብዛት የማህፀን ግድግዳ እንዲወፍር ያደርጋል፡፡
የእንጆሪ ወይም ፒንክ ቀለም ያለው የወር አበባ በጣም ዝቅተኛ የሆነ ኢስትሮጂን መጠን እንዳለው ያሳያል፡፡ የዚህ ሆርሞን ማነስ የሴት ሃፍረተ ሥጋ መድረቅ፣የፀጉር መነቃቀል፣ከፍተኛ ድካምና በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ እርካታ ላይ አለመድረስ ያስከትላል፡፡ ዝቅተኛ የኢስትሮጂን መጠን ያላቸው ሴቶች የወር አበባቸውን የሚመጣበት ቀን የተዘበራረቀ እና የዘገየ ነው፡፡
ሶስተኛው አይነት የወር አበባ ቀይ ቀለም ሲኖረው ይህ አይነት የወር አበባ ጤነኛ የሚባለው ነው ጊዜውን ጠብቆ መፍሰስ ይጀምርና ጊዜውን ጠብቆ ይቆማል፡፡

3. የወር አበባ አፈሳሰስ ሁኔታ
አንድ ጋሎን የሚያክል የሚመስል ደም በየወሩ ይፈስዎታል አማካይ የወር አበባ ፍሰት ግማሽ ኩባያ የሚያክል ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉም ሴቶች ከፍተኛ የደም መፍሰስ አያጋጥማቸውም ማለት አይደለም፡፡ ለረጂም ጊዜ የሚቆይ እና ብዛት ያለው ደም የሚፈስ ከሆነ የደም ማነስ፣ የማህፀን ግድግዳ እብጠት፣ የማህፀን በር ላይ ወይም ማህፀን ውስጥ እጢ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ እነዚህ አጋጣሚዎች እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ላይ በይበልጥ ይጨምራል፡፡
በትንሹ የወር አበባ የሚፈሳቸው ሴቶች የሆርሞን መቀየር እያደረጉ ወይም የምግብ እጥረትና ጭንቀት ያለባቸው ሴቶች ናቸው፡፡ ትንሽ ደም የሚፈሳቸው ሴቶች ቅድመ ዘመነ እርጠት ወይም እርጠት ምልክት ነው በተጨማሪም የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚወስድ ሴቶች ትንሽ የደም መፍሰስና ቀላል የወር አበባ ይኖራቸዋል፡፡

4. የወር አበባ ድግግሞሽ
የወር አበባ ድግግሞሽ ጥሩ የጤናዎትን ሁኔታ ጠቃሚ ነው ማዮ ክሊኒክ እንደሚጠቁመው የወር አበባ መጀመሪያ ካዩበት ከ21-35 ቀናቶች የሚመጣ ሲሆን ለመቆም ደግሞ ከ2-7 ቀኖች እንደሞፈጂበት እና እድሜ እየጨመረ ሲመጣ የሚቆምበት ቀን እያጠረና በይበልጥ እየተስተካከለ እንደሚመጣ ይናገራሉ፡፡
የወር አበባ የሚመጣበት ጊዜ በልጅነትዎ የተዘበራረቀ ከሆነ ወይም ለማቆም ከሰባት ቀን በላይ የሚፈጂበት ከሆነ ይህ ሊሆን የሚችለው በጣም የውፍረት መቀነስ ካለ፣ ጭንቀት፣ እርግዝና ወይም ለማህፀን ካንሰር የሚወስዱት መድሃኒት ካለ ነው በተጨማሪም የወር አበባ የሚመጣበት ቀን የተዘበራረቀ ሊሆን የሚችለው ከመጠን ያለፈ የአልኮል መጠን የሚጠጡ ከሆነ ነው፡፡ ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠቀም ጉበትን በመጉዳት የኢስትሮጂን እና ፕሮጀስትሮን ሆርሞን መስተጋብር ያዛባል፡፡ ለሴቶች የወር አበባ መዘበራረቅ ጤናማ ነገር ባይሆንም በአብዛኛው ጊዜ አስጊ አይደለም፡፡
5. የወር አበባ ካቆመ በኃላ መድማት
የወር አበባ ፈሶኝ ጨርሻለሁ ብለው ካሰቡ በኃላ እንደገና እየተቆራረጠ መፍሰስ ይጀምራል፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያ ለሚወስዱ ሴቶች የወር አበባ ፈሶ ካቆመ በኃላ እንደገና መፍሰስ ጤናማ ነው ነገር ግን ምንም አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳይወስዱ የሚፈስዎት ከሆነ በአፋጣኝ ሀኪምዎን ያማክሩ፡፡የሜዲፕላስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ይህ የደም መድማት የካንሰር ወይም ቅድመ ካንሰር ምልክት ሊሆን ስለሚችል አፋጣኝ መፍትሄ ያስፈልገዋል፡፡ በሌላ በኩል የሴት ሃፍረተ ስጋ ኢንፌክሽን እና የሆርሞን አለመመጣጠን ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

6. የወር አበባ መቅረት
የሴት ልጅ የወር አበባ ሲቀር በመጀመሪያ ወደ ህሊናችን የሚመጣው ነገር እርግዝና ነው ነገር ግን ለወር አበባ መቅረት/መዘግየት በጣም ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል አንድ ከእርግዝና ዉጪ የወር አበባ መቅረት ወይም በህክምና ቋንቋ አሚኖሪያ ይባላል ይህ ችግር ከአጠቃላይ የህብረተሰብ ክፍል በ4% ላይ ይከሰታል መገለጫዉም በሌላ ወቅት ጊዜውን ጠብቆ የሚመጣ የወር አበባ ለ6 ወር ወይም ከዚያ በላይ ማየት ሲያቆሙ ነው፡፡ ይህም የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚወስዱ ወይም ሆርሞን በሚወጉ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
በተጨማሪም በወፍራም ሴቶች፣ ለረጂም ጊዜ ጠንካራ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ እና የፋት(ስብ) መጠናቸው በጣም አነስተኛ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡ የጭንቅላት እጢ፣ የታይሮይድ እጢ ሲበዛ እና የእንቁላል ከረጢት ሥራ መቀነስ ለዚህ በሽታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ይደርጋሉ፡፡
በመጨረሻም የወር አበባ አንዱ የጤናን ሁኔታ ማወቂያ ዘዴ መሆኑን ሴቶች እህቶቻችን ልብ ሊሉት ይገባል፡፡

መልካም ጤንነት!!!

source

Via Danieltechnologist :  https://www.facebook.com/Danieltechnologist