Tomato
Tomato

የቲማቲም የጤና በረከቶች

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቲማቲም ለጤና ተስማሚ ናቸው ተብለው ከሚጠቀሱ የአትክልት ዓይነቶች መካከል አንዱ ነው።

ካንሰርን ይከላከላል፦ የካንሰር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ቲማቲም አዘውትረው በተመገቡ ቁጥር የበሽታውን መጠን በመቀነስ ወደ ጤነኝነት ደረጃ ሊያደርሳቸው ይችላል።

ቲማቲምን በሰላጣ  እንዲሁም አብስሎ በመመገብ ከአጥንት፣ ከማሕፀን፣ ከሆድ፣ ከጉሮሮ እንዲሁም ከጡት ካንሰር ለመዳን እንደሚረዳም ጥናቶች ያመለክታሉ።

የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል፦ የኮሌስትሮል መብዛት ችግር ያለባቸው ሰዎች በቀን ከሚመገቡት ምግብ ውስጥ ቲማቲም ቢጠቀሙ የኮሌስትሮል መጠናቸው እንዲቀንስ ያደርጋል።

ቲማቲም መመገብ የዓይናችንን የማየት አቅም እንዲጨምር ያደርጋል፦  በተለይም በጭለማ ሰዓት የማየት ችግር ያለባቸው ሰዎች ቲማቲምን አዘውትረው በመጠቀም እይታቸው የተሻለ እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ።

የደም ግፊት ችግርን ይከላከላል፦ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎቸ ቲማቲምን አዘውትረው ቢመገቡ የደም ግፊታቸውን መጠን ለመቆጣጠር ይረዳል።

የቆዳችንን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳናል፦ ቲማቲም መመገብ ጤናማ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል።

የስኳር ህመምን ለመቆጣጠር፦ በጭንቀት ምክንያት የሚከሰትን የስኳር ህመም ለመቆጣጠር ቲማቲምን አዘውትሮ መመገብም ይመከራል።

Source

Source: healthdigezt.com

Via: http://www.fanabc.com/index.php/fbc-shows/item/4650