brain
brain

አንጎላችንን ሊጎዱ የሚችሉ ልማዶች

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አንጎልን የሚጎዱ መጥፎ ልማዶችን እናካፍልዎ

1. ቁርስ አለመመገብ፦ ቁርስ አለመመገብ በሰውነታቸን  ውስጥ የሚገኘውን የደም ስኳር መጠን ስለሚቀንስ ለአንጎል የሚደርሰውን የምግብ መጠን በማስተጓጎል ለጉዳት ይዳርገናል።

2. በህመም ወቅት በቂ እረፍት አለማድረግ፦ በሚያመን ጊዜ በቂ እረፍት የማናደርገ ከሆነ በአንጎል ላይ ተጨማሪ ጫና እንዲኖር ያደርጋል ።

3. ሲጋራ ማጤስ

4. ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ።

5. የአየር ብክለት፦ የምንተነፍሰው አየር የተበከለ ከሆነና ለአንጎል የሚደርሰው የኦክስጅን መጠን ከቀነሰ በአንጎላችን ላይ ጉዳት ያስከትላል።

6. የእንቅልፍ እጦት፦ በቂ እንቅልፍ አለማገኘት አንጎላችንን ለጉዳት ይዳርጋል።

7. የአልኮል መጠጥ ማብዛት፦ በቀን የምንወስደው የአልኮል መጠጥ ከፍተኛ ከሆነ የአንጎል ህዋሶቻችንን ቀስ በቀስ ሊገድል ስለሚችል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

Source

ምንጭ፦ Dr. Honeliat