How to Get Clear Skin

ጥርት ያለ ቆዳን በአንድ ሳምንት ውስጥ ለመጎናፀፍ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአንድ ሳምንት ውስጥ ጥርት ያለ ቆዳን ለመጎናፀፍ የሚያስችሉ 5 ዘዴዎችን እንሆ።

1.አንድ ንፁህ ፎጣ ያዘጋጁ፣ ውሃ ያሙቁና ፎጣውን በመንከር ፊትዎን ለተወሰኑ ደቂቃዎች ይሸፍኑበት።

ይህም በፎጣው ላይ ያለው ውሃ እና እንፋሎት በቆዳዎ ቀዳዳዎች ላይ ያለውን ቆሻሻ ለማፅዳት ይጠቅማል።

ነገርግን ውሃው የፊትዎን ቆዳ እንዳይጎዳ ከሚፈለገው መጠን በላይ መፍላት የለበትም።

2.በመቀጠል እጅዎን አንቲባዮቲክ ሳሙናን በመጠቀም በሚገባ ያፅዱ ፤ ይህም በእጅዎ ላይ የሚገኙ ጀርሞችን ለማስወገድ ያግዛል፤ ፊትዎን በሚገባ ባለፀዱ እጆች ለማፅዳት መሞከር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላልና ጥንቃቄ ያድርጉ።

ፎጣውን ከፊትዎ ላይ በማንሳት የፊት ማፅጃ ካለዎት እርሱን በመጠቀም ለብ ባለ ውሃ ይታጠቡ፥ አልያም ፀረባክቴሪያ ሳሙናዎችን መጠቀም ይችላሉ።

3.ሁለት ማንኪያ ስኳርና ሁለት ማንኪያ የሞቀ ውሃን በትንሽ ሳህን ያዋህዱና በደንብ ከተዋሃደ በኋላ ተጨማሪ አንድ ማንኪያ ስኳር ይጨምሩበት፣ መልሰው ስኳርና ውሃውን በደንብ ያዋህዱት።

ከዚያም እጅዎን በንፁህ ውሃ ካረጠቡ በኋላ የቀላቀሉትን የስኳርና ውሃ ውህድ ፊትዎን በደንብ ይቀቡት።

ከተቀቡ በኋላ ጉንጭዎን፣ ግንባርዎን እና መላ ፊትዎን ክብ እየሰሩ ለአንድ ወይም  ለሁለት ደቂቃ ይሹት፣ ከዚያም ለብ ባለ ውሃ ያለቅልቁት።

4.ፊትዎን ታጥበው ሲጨርሱ 10 ማንኪያ ሎሚ እጅዎ ላይ በመጭመቅ ፊትዎን ለ10 ሰከንድ ያህል ያዳርሱት፣ ይህም በፊትዎ ቀዳዳ ላይ የቀሩ ቆሻሻዎችን ሙልጭ አድርጎ ለማስወገድ ፍቱን ነው፣ ይህ የማቃጠል ስሜት ስለሚኖረው ለተወሰኑ ሰከንዶች መታገስ ይኖርብዎታል፤ ይህም የቶነር አገልግሎትን የሚተካ ይሆናል።

5.በመጨረሻም ቀዝቃዛ ውሃን በመጠቀም ፊትዎ ላይ በመርጨት እንደቀድሞው ክብ እየሰሩ ለተወሰኑ ሰከንዶች ይሹት ፤ይህ ሂደትም ፊትዎ ላይ የሚገኙ ባክቴሪያዎችንና ቆሻሻዎችን በማስወገድ ንፁህ ፣ ለስላሳ እና ጥርት ያለ ቆዳ እንዲኖርዎት ያደርጋል።

ይህንን በየቀኑ ለአንድ ሳምንት በማድረግ ውጤቱን ማየት ይችላሉ።

source

– Via : http://www.wikihow.com/

Original Links
http://www.wikihow.com/Get-Clear-Skin-in-1-Week ተተርጉሞ የተጫነው፦ በሳሙኤል ዳኛቸው on  http://www.fanabc.com